የጨቅላ ህፃንን ለቅሶ መረዳት

ልጅሽ ማውራት እስኪጀምርና ባህሪውን እስክትረጂ ድረስ ብዙ ወራትን ይፈጃል። ታድያ በነዚህ ወራቶች ውስጥ ልጅሽ ስሜቱን የሚገልፀው በማልቀስ ይሆናል። ታድያ ልጆች ሊያለቅሱበት የሚችሉትን ምክንያቶች ማወቅ ችግሮችን ቶሎ ለመፍታት ይጠቅማል። ልጆች ሊያለቅሱባቸው የሚችሉባቸውን ምክንያቶችና ችግሩን ለማወቅ ልትከተይ የምትችያቸውን አማራጮች ማወቅ ይጠቅምሻል።

ርሀብ

ልጆች የሚያለቅሱበት ዋነኛውና የመጀመርያው ምክንያት መራብ ነው። በተለይ ሰውነታቸውን ማዘዝና ቱት ፈልገው ማግኘት ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ድረስ ሲርባቸው ማልቀስ የተለመደ ነው። ስለዚህም ልጅ ሲያለቅስ የመጀመርያው ውሳኔ ጡት መስጠት መሆን ይኖርበታል።

ምቾት ማጣት

ልጆች ሳይርባቸው ከተነጫነጩ ወይም ካለቀሱ ያልተመቻቸው ነገር አለ ማለት ነው። ምቾት ሊነሳ የሚችለው ሙቀት፣ ቅዝቃዜ ወይም የቆሸሸ ሽንት ጨርቅ ነው። አለባበሷንና ሽንት ጨርቋን በመቀየር ለቅሶዋን ማቆም ይቻላል።

ድካም

ህፃናት ሲደክማቸውና መተኛት ሲያቅታቸውም ያለቅሳሉ። ጡት ጠብቶና ምቾቱ ተጠብኮም ማልቀስ ካላቆመ ለማስተኛት መሞከር ሌላኛው አማራጭ ነው።

ህመም

የማያቋርጥ ጮክ ያለ ድምፅ ያለው ለቅሶ ብዙ ጊዜ ከህመም ጋር የተያያዘ ነውና ከላይ የተዘረዘሩትን አማራጮች ተጠቅመሽ ለቅሶውን ማቆም ካልቻል ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል። አብዛኞች ህፃናት በህክምና ምንም ምክንያት የማይገኝበት ግን ረዥም ሰአት የሚቆይ ለቅሶ ያለቅሳሉ። ምንም የጤና ችግር ከሌለባቸው ምናልባት ሆድ ቁርጠት ይሆናል ተብሎ ይገመታል። ጤነኛ መሆኑ በሃኪም ተረጋግጦ ግን ማልቀስ የማያቆም ከሆነ ሊያረጋጋው የሚችሉነገሮችን ተጠቀሚ፦ ልክ እንደ ገላ ማጠብና እሹሩሩ ማለት። እንደዚህ አይነት ለቅሶዎች ብዙ ጊዜ ከ 6 ወር በኋላ ይቀንሳሉ።
ምንም ያህል ብትጥሪ አንዳንዴ ለምን እንደሚያለቅሱ በፍፁም ላይገባሽ ይችላል። ይህ ታዲያ ሊያስጨንቅሽ አይገባም በጊዜ ሂደት የልጅሽን አመልና ፍላጎት በደንብ ትረጃለሽ።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ