ስኳር

በእርግዝና ወቅት የእንግዴ ልጁ የሚያመነጨው ሆርሞን በደም ውስጥ የስኳር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ጣፊያም በቂ ኢንሱሊን በማምረት ይህን የስኳር ክምችት ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን ጣፊያ የሚያመርተው የኢንሱሊን መጠን ካነሰና በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከበዛ ለዚህ አይነቱ የስኳር በሽታ ይዳርጋል፡፡ የዚህ አይነቱ የስኳር በሽታ በእርግዝና ጊዜ ብቻ የሚከሠት ሲሆን የልጅሽን ጤንነት በማይነካ መልኩ ሀኪምሽ የሚነግርሽን በጥንቃቄ በመተግበርና ቀን በቀን የደምሽን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ጤነኛ ልጅ መውለድ ትችያለሽ፡፡ ልጅሽን ከወለድሽ በኋላ የሚጠፋ ይሆናል፡፡ አንዳንዴ ሁለተኛ የሚባለውን የስኳር በሽታ አይነት ሊያመጣ ቢችልም የመከሰት እድሉ ግን በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ የስኳር መጠን መጨመር የደም ግፊት መጨመር፤ ፕሪ-ኢክላምዚያ፤ ያለጊዜ መውለድንና በቀዶ ጥገና መውለድን በእናትየው ላይ ሲያስከትል ህፃኑ ላይ የልብ፣ ያጥንት እና የነርቭ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ከዚህም ባለፈ የፅንሱን መጠን ሊያተልቅና የስኳር መጠኑን ደሞ ሊያሳንስ ይችላል። ተገቢው ህክምና ካልተደረገና የስኳር መጠን መጨመር ፅንሱ በማህፀን እያለ ህይወቱ እንዲያልፍም የማረግ እድል አለው።

ምልክቶች

የስኳር በሽታ የተለየና ወጣ ያለ ምልክት አያሳይም። ለዛም ነው የትኛዋም ነብሰ ጡር የስኳር ምርመራ ማድረግ የሚኖርባት። ከታች የተዘረዘሩት ዋና የሚባሉት ምልክቶች ናቸው።
 • የማየት ችግር ወይም ብዥታ
 • የእጅ ወይም እግር ማበጥ
 • ውሃ ቶሎ ቶሎ መጥማት
 • ሽንት ቶሎ ቶሎ መሽናት
 • ድካም
✸ ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩብሽ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብሻል።

ማንን ያጠቃል

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምክንያቶች ተጋላጭነትን ይጨምራሉ ።
 • ከእርግዝና በፊት የተከሰተ ከፍተኛ ክብደት
 • የበሽታው ተጠቂ ሳትሆን የስኳር መጠኗ ከፍተኛ ከሆነ
 • አስቀድሞ በነበረ እርግዝና የስኳር ተጠቂ ከነበረች
 • በቤተሰብ ውስጥ የስኳር ታማሚ ካለ
 • ህክምና

  ለበሽታው ተጋላጭነትሽ ከፍተኛ ከሆነ ህክምናሽን የሚከታተለው ሀኪም ቀደም ብሎ ምርመራውን ያካሂዳል፤ ካልሆነ ግን ከ 24 እስከ 28ተኛው ሳምንት ውስጥ ምርመራ ይደረግልሻል፡፡ የስኳር መጠንሽ ከመደበኛው በላይ ከሆነ በየጊዜው ተከታታይ ህክምና እየተደረገ የሚስተካከልበት ወይም ጉዳት የማያስከትልበት መንገድ ይፈለጋል። የስኳር ተጠቂ ከሆንሽ ሀኪምሽ በሚመክርሽ መንገድ አመጋገብሽንና የአካል እንክስካሴሽን ማስተካከል ይኖርብሻል። እንደ ስኳር መጠንሽም ተጨማሪ መዳኒቶችን መውሰድ ሊኖርብሽ ይችላል።
  Share on facebook
  Share on google
  Share on twitter

  አስተያየት

  መዝጊያ