ተጨማሪ ማእድናት

ምንም እንኳን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ሰውነትሽ የሚያስፈልገውን ንጥረ ነገር ለመስጠት ቢችልም አንዳንድ ንጥረ ነገሮች በምግብ ውስጥ የሚገኙበት መጠን አነስተኛ በመሆኑና የሚያስፈልገው መጠን ግን በጣም ብዙ በመሆኑ በተጨማሪ የማእድን እንክብሎችን መውሰድ ሊኖርብሽ ይችላል። የምትወስጅው የእንክብል መጠን ባለሽ የአመጋገብ ተለምዶና የጤና ሁኔታ ይወሰናል። በኛ ሀገር የሚሰጡት ንጥረ ነገሮች ፎሊክ አሲድ፣ ካልሲየምና አይረን ናቸው።
suppliment

ፎሊክ አሲድ

የፎሊክ አሲድ እጥረት በጭንቅላትና በህብረሰረሰር ላይ ጉዳትን ያስከትላል። ይህም የአጥንት መጉበጥ፣ ያለቦታው መብቀልና ጭራሹንም አለማደግን ይጨምራል። እነዚህ ችግሮች በመጀመርያው ሶስት ወራት ውስጥ በመሆኑ የሚፈጠሩት በእቅድ የምትወልጂ ከሆነ ከማርገዝሽ በፊት ካልሆነ ደግሞ ማርገዝሽን እንዳወቅሽ ለ3 ተከታታይ ወራት መውሰድ ይኖርብሻል።

ካልሲየም

ካልሲየም ከብዙ ምግቦች መገኘት ቢችልም መጠኑ አነስተኛ ከሆነ ተጨማሪ የተዘጋጀ እንክብል መውሰድ ያስፈልጋል። የካልሲየም እጥረት የልጅሽ አጥንት እድገት ላይ ተፅእኖ ስለሚያሳድር እንደ ወተትና የወተት ተዋፅኦ፣ አበባና ጥቅል ጎመን፣ ቆስጣና በሎቄ በመብላት የልጅሽን አካላዊ እድገት መጠበቅ አለብሽ። በተፈጥሮ ሰውነትሽ ወደፅንሱ ስለሚያደላና ያለሽን ካልሲየም ወደልጁ በመውሰድ ያንቺን አጥንት ሊያዳክምና ፅንሱን መሸከም እንዲያቅትሽም ሊያረግ ይችላል።

አይረን/ብረት

የብረት እጥረት ያለባት ነብሰጡር ለደም ማነስ ተጋላጭ ነች። ደም ማነስ ማለት የቀይ የደም ሴል እጥረት ማለት ሲሆን ድካምንና ማዞርን፣ ትንፋሽ ማጠርንና የልብ ምት መጨመር እንዲሁም እራስ መሳትን ሊያስከትል ይችላል። በሌላ በኩል ደምሽ እያነሰ ነው ማለት ለልጅ በቂ አየርና ምግብ ማድረስ አትችይም ማለት ነው። ይህ ደግሞ ያለጊዜው ወሊድን ሊያስከትል ይችላል። የብረት ንጥረ ነገር እንክብሎች ከ 3 ወር እስከ 9 ወር ድረስ ማለትም ለ6 ወራት መወሰድ ይኖርበታል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ