ተጨማሪ ምግብ

ልጅሽ 6 ወር ሲሆነው ተጨማሪ ምግብ ጀምሪለት፡፡ ተጨማሪ ምግብ የሚያስፈልገው:
 • ከ6 እስክ 24 ወራት (2 ዓመት) ያለው የሕፃናት የአመጋገብ ሥርዓት የጤንነታቸው የአካልና የአእምሮ ዕድገታቸው ዋነኛ መሠረት በመሆኑ
 • ከ6 እስከ 24 ወራት (2 ዓመት) ያለው የአመጋገብ ሥርዓት ከቤተሰብ ጥቅም አልፎ ሀገራችን ጤነኛና ምርታማ ዜጋ ከማፍራት አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ ስላለው
 • በአብዛኛው የሕፃናቱ የምግብ መጎዳትና መታመም የሚጀምረው ከ6ወር በኋላ ሕፃናት ለዕድገት በቂ ወዳልሆነ የአመጋገብ ሁኔታ ሲገቡ በመሆኑ
 • ከ0 እስከ 2 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ ካልሆነ አመጋገብ የተነሳ የሕፃናት መቀጨጭ እና የእእምሮ ለትምህርት ብቁ ያለመሆን ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ ለመመለሰ የማይቻል በመሆኑ ነው
ታዲያ ተጨማሪ ምግብን አስቀድሞም ሆነ ዘግይቶም መጀመር ችግር ሊያመጣ ይችላል።
  ተጨማሪ ምግብን ሕፃናት ስድስት ወር ሳይሆናቸዉ ቀደም ብሎ መጀመር ጉዳትን ያስከትላል
 • ሕፃናት የጡት ወተትን በደምብ እንዳይጠቡ ያደርጋል
 • ተጨማሪ ምግቡ እንደጡት ወተት ንጹህ ስለማይሆን በተቅማጥ በሽታ የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡
  ተጨማሪ ምግብን ሕፃናት ስድስት ወር ካለፋቸው በኋላ ዘግይቶ መጀመር ጉዳት ያስከትላል
 • ሕፃናት የሚያስፈልጋቸዉን ኃይል እና ንጥረ ነገር ለሟሟላት መመገብ ያለባቸውን ተጨማሪ ምግብ አያገኙም
 • የሕፃናት በምግብ እጥረት እና የንጥረ ነገሮችን አለመመጣጠን ችግር የመከሰት ዕድልን ይጨምራል፡፡ እንዲሁም እድገታቸውን ይቀንሳል ወይም ያቆማል፡፡

ለሕፃኑ የበለፀገ ምግብ አዘገጃጀት

 • ለገንፎ ዱቄት ዝግጅት: ሦስት እጅ እህል (በቆሎ፡ማሽላ፡ጤፍ፡ገብስ ወይም ማንኛውም በአካባቢዉ የሚገኝ እህል)/ስራስር (ቆጮ ቡላ የመሳሰሉት) እና አንድ እጅ ጥራጥሬ (አተር፤ ሽንብራ፡ ባቄላ እና ምስር) በማደባለቅ የተዘጋጀ ዱቄት ማምጣት፡፡
 • ከላይ የተጠቀሰውን የእህል ዝግጅት በመጠቀም ለሰለስ እና ወፈር ያለ ገንፎ ማዘጋጀት
 • የተዘጋጀውን ገንፎ የበለጠ ጠቃሚ ለማድረግ ከዚህ የሚከተሉትን የምግብ ዓይነቶች በተገኘ ጊዜ ሁሉ አንድ ወይም ሁለት ዓይነት ምግቦችን መጨመር
   • አንድ የሻይ ማንኪያ የቋንጣ ዱቄት
   • ልሞ የተከተፈ አትክልት ጎመን ካሮት
   • ዕንቁላል
   • በወተት ማገንፋት
 • በተዘጋጀው ገንፎ ውስጥ ትንሽ ቅቤ ወይም ዘይት እና አዮዲን ያለው ጨው መጨመር
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

አስተያየት

መዝጊያ