አደገኛ ምልክቶች

እርግዝና በሰላም የሚያልፉ የተፈጥሮ ሂደት ቢሆንም አንዳንድ ሴቶች ላይ ያልተጠበቀ ችግር ሊያጋጥም ይችላል። የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ እነዚህ ያልተጠበቁ ችግሮች ሲያጋጥሙ ቶሎ መፍትሄ ለመስጠት ይጠቅማል። ስለዚህ አደገኛ ምልክቶች ተብለው የተዘረዘሩት ወይም በያንዳንዱ በሽታዎች ስር የተዘረዘሩትን ልዩ ምልክቶች ካየሽ አደገኛ ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግና የህክምና እርዳታ ማግኘት ይጠበቅብሻል።

ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አደገኛ ምልክቶች ውስጥ አንድ ወይም ከዛ በላይ ካጋጠመ በጽንሱ እና በእናቱ ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር ሊኖር ስለሚችል በቶሎ ወደ ሐኪም መሄድ ያስፈልጋል:-
 • እጅና እግር እብጠት
 • ያልተለመደ የሆድ ህመም፤
 • በብልት በኩል ከባድ የደም መፍሰ
 • ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት፤
 • እይታ ብዥ ማለት
 • ተደጋጋሚ ትውከት
 • የማያቋርጥ ራስ ምታት፤
 • የፅንሱ እንቅስቃሴ መቆም
 • ብዛት ያለውና የሚያሳክክ ቢጫ ወይም ነጭ የብልት ፈሳሽ
እነዚህ አደገኛ ምልክቶችና ተያያዥ ችግሮች:-
 • እናትየው ከ18 ዓመት በታች ከሆነች፤
 • እናትየው ከ35 ዓመት በላይ ሆና ለመጀመሪያ ጊዜ ካረገዘች፤
 • የበፊቱን እርግዝና በቀዶ ጥገና ሕክምና /ኦኘራሲዮን/ ከተገላገለች
ሊበረቱ ስለሚችሉ የቅድመ ወሊድ ክትትሉ እጅግ ጠንካራ መሆን ይኖርበታል። ከላይ የተዘረዘሩት አደገኛ ምልክቶች ሊያስከትሉት የሚችሉትን ዋና ዋና ችግሮች ከታች ከተዘረዘረዘሩት ማውጫዎች ላይ በመምረጥ ማንበብ ይቻላል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

This Post Has One Comment

አስተያየት

መዝጊያ