ኤች.አይ.ቪ ኤድስ

በእርግዝና ወቅት የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ምርመራ ማድረግ እጅግ አስፈላጊና በሽታው ካለብሽ ወደልጅሽ እንዳይተላለፍ የምታደርጊበት የመጀመርያው እርምጃ ነው። ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በእርግዝና ጊዜ፣ በምጥና በወሊድ ጊዜ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ ጡት በማጥባት ጊዜ ከናት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል። የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ምርመራ አድርገሽ በሽታው ከተገኘብሽ ጤነኛ ልጅ ለመውለድ የፀረ ኤችአይቪ መድሃኒት መውሰድ መጀመር ይኖርብሻል። በወሊድ ጊዜም ልጁ ካንቺ ደም ጋር ንክኪ እንዳይኖረውና በሽታው እንዳይዛመድበት በጤና ተቋም መውለድ ይኖርብሻል።

ምልክቶች

ኤችአይቪ/ኤድስ ቶሎ ምልክት የማያሳይ በሽታ ነው። በሽታው ሰውነታችን ውስጥ በደንብ ከተሰራጨ ግን ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል
  • የአፍ ቁስለት፣ የጉሮሮ መድረቅ
  • ቶሎ ቶሎ መታመም
  • እራስ ምታትና ሲተኙ ማላብ
  • የክብደት መቀነስና የፀጉር መብነን
  • ደረቅ ሳል፣ ተቅማጥ፣ ትኩሳት
  • አቅም ማጣት
  • በሰውነትና በመራቢያ አካል ላይ ሽፍታ
  • አጥንት መገጣጠምያና ነርቭ ህመም

ማንን ያጠቃል

ኤችአይቪ/ኤድስ በግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ ከእናት ወደልጅ (በእርግዝና፣ በምጥ፣ በወሊድ እና በጡት ማጥባት ወቅት)፣ በደም በተበከሉ ስለት ያላቸው ነገሮችና በኤች አይቪ የተበከለ ደም በመቀበል (blood transfusion) ይተላለፋል። ለነዚህ ሁኔታዎች የተጋለጡ እናቶችና ህፃናት በሙሉ በበሽታው የመያዝ እድላቸው ሰፊ ነው።

ህክምና

ኤችአይቪ/ኤድስን የሚፈውስ መዳኒት ባለመኖሩ በኤችአይቪ/ኤድስ ላለመያዝ መጠንቀቅ ብቸኛው አማራጭ ሲሆን አንቺ ካለብሽ ግን ቢያንስ ወደልጅሽ ላለማስተላለፍ በቂ የቅድ መወሊድ ክትትል፣ በህክምና ተቋም መውለድና ከወሊድ በኋላም በቂ የድህረ ወሊድ ክትትል ማረግ ይኖርብሻል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ