ከወሊድ በኋላ እራስን መጠበቅ

አራስ ስትሆኚ ልጅሽን መንከባከቡ እንዳለ ሆኖ እራስሽንም መጠበቅ ይኖርብቻል። ብታምኚም ባታምኚም ጤነኛ ሆኖ የተወለደም ህፃን እናቱ ጤነኛ ካልህነች በሒወት የመቆየት እድሉ በጣም አናሳ ነው። እራስሽን ስትጠብቂ ልጅሽንም እየጠበቅሽ እንደሆነ አስቢ። ጥንካሬሽ እስኪመለስና በወሊድ ምክንያት የተጎዳው ሰውነት እስኪጠገን ድረስ፦
  • በቂ እረፍት አድርጊ: ባገኘሽው አጋጣሚ ሁሉ ተኚ፤ ድካምሽ እንዲቀንስ ይረዳሻል። አራስ ልጆች በየ2 ወይም 3 ሰአቱ መመገብ ስለሚኖርባቸውና ስለሚነቁ በቂ እንቅልፍ እንድታገኚ ልጅሽ በተኛ ቁጥር አብረሽ ተኚ። በቀዶ ጥገና ከወለድሽ ግን ቁስሉ እንዲያገግም መንከሳከስ ስላለብሽ እቤት ውስት መረማመድ ይኖርብሻል።
  • የተመጣጠነ ምግብ ተመገቢ: በወሊድ ጊዜ ሰውነትሽ ስለሚጎዳ ሰውነት ሊጠግን የሚችሉ ምግቦችን ተመገቢ። ጥሩው ነገር በሃገራችን ሴት ልጅ ስትወልድ መታረስ ባህላችን ስለሆነ ብዙም የሚያሳስብሽ ጉዳይ አደለም። ስትመገቢ ግን የእንስሳት ተዋፅኦ፤ እህል፤ ቅጠላቅጠልና ፍራፍሬን አካተሽ መብላት ይኖርብሻል። በወለድሽ የመጀመርያ ሳምንታት መመገብ ሊከብድሽ ወይም ሊያስጠላሽ ይችላል ነገር ግን ላንቺ ብቻ ሳይኖን ለልጅሽም ጡት ማጥባት የምትችይው ስትመገቢ በመሆኑ ስለጣፈጠሽ ሳይሆን ስለሚያስፈልግሽ ተመገቢ። የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ከዚህም አልፎ በእርግዝና ሰአት የጨመርሽውን ክብደት በቀላሉ እንድትቀንሺ ይረዳሻል።
  • እርዳታን ተቀበይ: እናት ሆነሽ ሙሉ እረፍት ልትወስጂ የምትችይው በዚህ ወቅት ብቻ ነውና ጊዜሽን ተጠወሚበት። ሁሉንም ነገር እራስሽ ማድረግ የምትፈልጊ አይነት ሰውም ብትሆኚ ይህን ወቅት ግን ቤተሰብ፤ ሰራተኛ ወይም ጓደኛ እንዲያግዝሽ ፍቀጂ። ሰውነትሽ ሳያገግም ስራ መስራት ለጊዜው ባይታወቅሽም ጊዜ ሲገፋ ከፍተኛ የወገብ ህመም ሊያስከትልብሽ ይችላል።
  • እንቅስቃሴ አድርጊ: አንዴ ተኚ አንዴ እንቅስቃሴ አርጊ ምንድነው?እንዳትዪ። ሰውነትሽ ሲጠነክር እንቅስቃሴ ማድረግ ተገቢ ነው። ውፍረት ለመቀነስና ወደነባር የህይወት ዘይቤሽ እንድትመለሺ ይረዳሻል።
  • ንፅህናሽን ጠብቂ: ከወለድሽ በኋላ ባሉት ተከታታይ ሳምንታት አንቺም ልጅሽም ለኢንፌክሽን ተጋላጭነታቹ በጣም ሰፊ ነው። ስለዚህም የራስሽን ንፅህና መጠበቅ ይኖርብሻል። በምጥ ከወለድሽና እስቲች ከተሰራሽ ወይም ልጁ ሲወጣ ሰንጥቆሽ ከሆነ ሞቅ ያለ ውሃ ውስጥ ጨው በመጨመር ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ታጠቢ። ይህ እንፌክሽን እንዳይፈጠር ይረዳል። ብዙ ስለምትተኚና ስለምታጠቢ ገላሽንም ቢያንስ በየሶስት ቀኑ ታጠቢ። ስትታጠቢ በሞቀ ውሃ ሆኖ ብርድ ሊያገኝሽ የማይችልበት ቦታ መሆን አለበት። ሌላው ደሞ ከወሊድ በኋላ ለተወሰኑ ቀኖችም ደም መፍሰስ ይኖራል። ሞዴስ ከመጠቀም ጨርቅከምትተኚበት ስር ማነጠፍ ይመከራል ይህም ኢንፌክሽንን ለመቀነስ ይረዳል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ