ወሊድ

ወሊድ ላንቺ የእርግዝና መጨረሻ ለልጅሽ ደሞ ከ 9 ወር ቤቱ ወቶ አለም ላይ አዲስ ህይወት የሚጀምርበት ቀን ነው፡፡ የወሊድ አስፈሪውና አስጨናቂው ክፍል ምጥ ነው፡፡ መውለጃሽ ከመድረሱ አንድ ወር በፊት ለወሊድ የሚያስፈልጉሽን ነገሮች ማዘጋጀት ይኖርብሻል፡፡ ቤትም ወለድሽ የህክምና  ተቋም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ቀድሞ ማዘጋጀት ምጥ በሚጀምርሽ ሰአት ሁኔታዎችን በቀላሉ መንገድ እንድትወጪ ያደርግሻል፡፡
 • የምትወልጅው በክህምና ተቋም ከሆነ የተቋሙን ስልክ ቁጥር አድራሻና የስራ ሰአት ማወቅ (መዝግቦ ማስቀመጥ)
 • ቤት የምትወልጂ ከሆነ የአዋላጅሽን ስልክ ቁጥርና መገኛ ሰአትን መመዝገብ
 • ወደ ሆስፒታል የምትሄጅበትን ወይም አዋላጅሽ ወደ ቤት የምትመጣበትን መንገድ ማመቻቸት ይህ የአንቡላስ ቁጥር፣ የዘመድ ስልክ ቁጥር ወይም  የኮንትራት ታክሲ ስልክ ቁጥር ሊሆን ይችላል።
 • ቤት የምትወልጂ ከሆነ የልጁ እትብት የሚቆረጥበት አዲስና ንፁህ ምላጭ እንዲሁም እትብት ማሰሪያ ክር ማዘጋጀት አለብሽ፡፡በወሊድ ሰአት ምላጩ መቀቀል ይኖርበታል።
 • በየትኛውም ቦታ ብትወልጂ ለልጅሽ ልብስ የሽንት ጨርቅ (ዳይፐር)፣ የቂጥ መጥረጊያ፣ መታቀፊያ፣ የገላ መታጠቢያ (መዘፍዘፊያ)፣ የገላ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ፣ ማዘጋጀት።
 • ላንቺ ነጠላጫማ፣ ካልሲ፣  የወሊድ ልብስ (ቀሚስ ሆኖ ጡት ለማጥባት የሚመች) መቀየሪያ ፓንቶችና ሞዴስ (ከወሊድ በኋላ ለተወሰነ ቀን ደም ስለሚፈስሽ)
 • በኦፕራስዬን ከወለድሽ ጡት ማጥባት ስለማትችዮ ጡጦ ማዘጋጀት አለብሽ
 • ከወለድሽ በኃላ የምትታረሽበትን እህል
 • ለትራንስፖርት ለሆስፒታል ወጪ የሚሆን ገንዘብ ማዘጋጀት
 • በምጥና ወሊድ ጊዜ አብሮሽ ቢሆን የሚሻል ሰው መምረጥና ማዘጋጀት
Pregnancy and birth cartoon vector illustration. Pregnant mother young girl in hospital bed with newborn baby new mom with child. Maternity and medical infographic isometric people design
what-to-expect-after-giving-birth-in-a-hospital

የወሊድ ቦታ

አብዛኛው የሀገራችን ህብረተስብ በተለይ በገጠሪቷ ኢትዬጵያ  የሚኖሩ ሴቶች የሚወልዱት በቤታቸው ነው፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚታየው የጤና ሽፋን ማነስ፣ ሴቶች በህክምና ቦታ የሚደርስባቸው እንግልትና በወሊድ ሰአት የሚከናወኑ ባክላዊ ሂደቶች በህክምና ቦታ አለመኖራቸው ነው፡፡ በአሁን ሰአት የጤና ማኒስቴር በእናትና ህፃናት ጤንነት ላይ ብዙ እየሰራ በመሆኑ ማንም እርጉዝ ሴት ክብሩዋን በማይነካ መልኩ በየትኛውም ህክምና ተቋም የቅድ-መወሊድ፣ ወሊድና ድህረ-ወሊድ ክትትል እንድታገኝ ደንግጓል፡፡ አንድ ነብሰ-ጡር በህክምና ቦታ ስትወልድ ቤቷ ሊደረግላት የሚችሉትን ባህላዊ ነገሮች በሙሉ በህክምና ጣቢያው እንደደረግላት እየተደረገም ነው፡፡ በምጥ ሰአት የህክምና ባለሙያዎች በጥንቃቄና አክብሮት በተሞላበት መንገድ እንዲያስተናግዱም ተደርጓል፡፡

የምትወልጂበት ቦታ በእርግዝና ሰአት ባለሽ ጤንነት ይወሰናል፡፡ ሆኖም ወሊድ ሙሉ ለሙሉ በህክምና ተቋም ቢሆን ይመከራል፡፡ በቅድመ-ወሊድ ክትትልሽ ጊዜ ምንም ችግር ስላልታየብሽ ቤትሽ ብትወልጂ የከፋ ችግር ላይመጣብሽ ይችላል፡፡ ሆኖም ቀድመው የማይታዩ ግን በምጥና በወሊድ ሰአት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች ያንቺንም የልጅሽንም ህይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡ እናቶቻችን ቤት ነው የወለዱን ምንም አንሆንም በሚል ምክንያት ቤት ውስጥ መውለድ ተመራጭ ተደርጎ ቢወሰድም ማወቅ ያለብሽ የሁሉም ሰው እርግዝና፤ ምጥና ወሊድ የተለያየ መሆኑን ነው፡፡

እርግዝናሽ ሰላማዊ ቢሆንም በምጥ ሰአት ልጅሽ ቢታፈንና ማማጥ ባትችይ፣ በጭንቅላቱ መምጣት ሲገባው እጁ ወይም እግሩ ቢቀድም፣ ልጁን ከወለድሽ በኃላ የእንግዴ ልጅ በሰአቱ ባይወጣ፣ ከወሊድ በኃላ ብዙ ደም ቢፈስሽ፣ ምጥ ቢበዛብሽና ማማጥ ባትችይ እና የመሳስሉ ችግሮች ቢያጋጥሙሽ የህክምና እርዳታ ያስፈልግሻልና በተቻለሽ አቅም ሆስፒታል ለመውልድ አስቢ፡፡ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የማይመች ቦታ ከሆንሽ የሰለጠነች የመንደር ውስጥ አዋላጅ መምረጥ አለብሽ፡፡

መጀመሪያ ላይ እንደተገለፀው በቅድመ-ወሊድ ክትትልሽ ጊዜ የተወሳሰቡ (አደገኛ) ችግሮች ከታዩብሽ በምን አይነት የህክምና ተቋም መውለድ እንዳለብሽ ይነገርሻል። ለምሳሌ የደም ግፊትሽና የስኳር መጠንሽ እጅጉን ከፍ ካለ ማማጥ ስለማትችይና በኦፕራሲዬን መውለድ ስላለብሽ ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል ትላኪያለሽ፡፡ እንደ ጤናሽ ሁኔታ የምትወልጂበት ቦታ ከጤና ኬላ አንስቶ እስከ ሪፈራል ሆስፒታል ድረስ ሊሄድ ይችላል፡፡ የመውለጃ ቦታሽን ስትወስኚ ያንቺና የልጅሽን ጤና ያማከላ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ይረዳሽ ዘንድ የቅድመ-ወለድ ክትትልሽን ማድረግ ይኖርብሻል፡፡ ያሉሽን ጥያቄዎች በሙሉ ያለሀፍረት መጠየቅና ሀኪም የሚልሽን ጠንቅቀሽ መስማት ይኖርብሻል፡፡

images

የውሊድ እክሎች

በምጥ/ወሊድ ሰአት ቀድመው የተተነበዩ ወይ ደሞ ድንገተኛ የሆኑ ውስብስብ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ
 • ያለጊዜ መውለድ: ከ37 ሳምንት በፊት የሚወለዱ ህፃናቶች አብዛኛዉ የሰዉነታቸዉ ክፍል ሙሉ ለሙሉ ስላላደገ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ያለጊዜያቸዉ የተወለዱ ህፃናት በህፃናት ማቆያ ክፍል የሚደረጉትም ሰዉነታቸዉ ከናታቸዉ ማህፀን ዉጪ የመኖር አቅም ስለሌለዉ ነዉ። እንደነዚህ አይነት ህፃናቶች በሽታን የመከላከል አቅማቸዉ፤ የአተነፋፈስ ሂደታቸዉ፤ የልብ ምታቸዉና የአመጋገብ ስርዓታቸዉ በበቂ ሁኔታ ስላልጠነከረ ቋሚ የህክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡
 • ረዥም ምጥ: ምጥ እየጨመረ በሄደ ቁጥር እናትየውም ልጁም አደጋ ላይ እየወደቁ ይሄዳሉ፡፡ የምጥ ከልክ በላይ መርዘም ቀዶ ጥገና ለመደረግ አንደኛዉ ምክንያት የሆነዉም የከፋ አደጋ እንዳያመጣ ነዉ
 • ህፃኑ አመጣጡ በጭንቅላቱ ካልሆነ መሳሪያ መጠቀም ያለበለዚያ ቀዶ ጥገና ማድረግ ግዴታ ይሆናል
 • የእሽርት ዉሃ ምጥ ከመጀመሩ አስቀድሞ ከፈሰሰና ከ12-24 ሰዓት ዉስጥ ልጁ ካልተወለደ በህፃኑ ላይ ኢንፌክሽን ያመጣል
 • እትብቱ ከልጁ ቀድሞ ከወጣ ወደ ልጁ የሚሄደው ደም ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ለልጁ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በሙሉ፤ አየርና ምግብን ጨምሮ፤ የሚደርሰዉ በእትብቱ በመሆኑ እትብቱ ቀድሞ ከወጣና ቦታው ከተዘጋ ልጁ ሊሞት ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ አፋጣኝ ህክምና የሚያስፈልገዉ ነዉ
 • የእንሽርት ዉሃዉ በአስቸጋሪ ምጥ ወይም በቀዶ ጥገና ጊዜ እናትየዉ የደም ዝዉዉር ዉስጥ ከገባ የልብ ምትን ሊጨምር አጓጉል አመታት እንዲመታ፣ እንድትንቀጠቀጥና የልብ ድካም እንዲይዛት ሲከፋም ለሞት ሊያደርሳት ይችላል
 • በእርግዝና ሰዓት የሚፈጠር የደምግፊት መጨመር የእንግዴ ልጁ ያለጊዜዉ ከማህፀን ግድግዳ ላይ እንዲለቅ ሊያደርግ ይችላል 
 • የእንግዴ ልጁ ከማህፀን በሚላቀቅበት ጊዜ ማህፀን ካልተኮማተረ ከማህፀን ጋር የሚገናኘዉ የደም ቱቦ በኩል ብዙ ደም ይፈሳል፡፡ ይህም አብዛኛዉ በህክምና ቦታ የማይወልዱ እናቶች የሚሞቱበት ምክንያት ነው 
 • ልጁ ከተወለደ በኋላ እትብቱ ዉስጥ ከቀረ፣ እትብቱ የማህፀን በር ላይ ከተቀመጠና ልጁ እንዳይወጣ ካገደዉ፣ እትብቱ ከማህፀን ዉጪከሆነና የህፃኑ አንገት ላይ ከተጠመጠመ በወሊድ ጊዜ እናትየዉንም ልጁንም አደጋ ላይ ይጥላል   
 • ልጁ በሚወጣ ጊዜ የዉጨኛዉ የብልት ክፍል መሰንጠቅ ወይም መቀደድ
 • የጽንሱ ልብ ምት መቀነስ ወይም መጨመር: ከ110 ማነስ ወይም ከ160 መብለጥ 
 • የልጁ መጠን ከፍተኛ መሆን ወይም በጣም ማነስ: (2.8 ኪሎ በታች ወይም ከ4 ኪሎ በላይ)
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ