ውርጃ

ውርጃ ማለት በመጀመሪያዎቹ 20 ሳምንታት ውስጥ እርግዝና ሲቋረጥ ማለት ነው፡፡ በአብዛኛው ጊዜ ከ 12 ሳምንት በፊት የሚከሰትም ነው። ብዙዎቹ ውርጃዎች የሚፈጠሩት በፅንሱ ላይ በሚኖር የስነፍጥረት / GENETICS / ችግር ምክንያት ነው፡፡ በአብዛኛው የዚህ አይነት ችግር ከናትየው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም፡፡ በሌላ በኩል የእናትየው የጤና ሁኔታ ውርጃ እንዲፈጠር መንገድ ሊፈጥር ይችላል።

ምልክቶች

አብዛኛው ምልክት ውርጃው ሲፈጠር የሚታይ በመሆኑ ባፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።
 • ቀለል ብሎ ጀምሮ እየከበደ የሚሔድ የደም መፍሰስ
 • በወር አበባ ጊዜ የሚሰማ አይነት ቁርጠት
 • የሆድ ህመም
 • ትኩሳት
 • የጀርባ ህመም
 • ከመጠን ያለፈ ድካም
 • ብርድ ብርድ ማለትና የህመም ስሜት

ማንን ያጠቃል

ከታች የተዘረዘሩት ምክንያቶች የሚታይባት ነብሰ ጡር ለውርጃ ተጋላጭ ትሆናለች
 • ኢንፌክሽን
 • ዝቅጠኛ በሽታን የመከላከል አቅም
 • የስኳር መጠን መጨመር
 • የማህጸን ችግር
 • የማህፀን በር ፅንስ የመሸከም አቅም ማነስ
 • እድሜ ከ 35 አመት በላይ መሆን
 • አስቀድሞ የነበረ ተደጋጋሚ ውርጃ
 • እርግዝናው በማህፀን የሚቀበር (አይ ዩ ዲ) የእርግዝና መከላከያ እየተጠቀምሽ ከተፈጠረ
 • የምታጨስ ነብሰ ጡር

ህክምና

ውርጃን መከላከል ከባድ ነው ምክንያቱም ውርጃ እርግዝናው ጤናም ባለመሆኑ የሚከሰት ሰለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ምልክቱ ቀድሞ በሌላ ምርመራ ላይ ከተገኘ የተለያዩ የህክምና መንገዶችን በመጠቀም ውርጃ የመፈጠር እድሉን ማጥበብ ይቻላል፡፡ ውርጃ እንደተከሰተ ከተጠረጠረ ወይም ምልክት ከታየ የማህፀን ምርመራ፣ አልትራሳውንድ ወይም የደም ምርመራ በማድረግ እርግጠኛ ለመሆን ይሞከራል። ውርጃ ከሆነና ፅንሱ ሙሉ ለሙሉ እንዲወጣ ይደረጋል። የደም መፍሰሱ እንደቆመ ነባር ህይወት መቀጠል ይቻላል። አንዲት ነብሰ ጡር ውርጃ አጋጥሟታል ማለት መውለድ አትችልም ማለት አይደለም። ሆኖም ውርጃ ካጋጠመሽ ድጋሚ ለማርገዝ የህክምና ውጤትሽ እና የባለሙያ አስተያየት ቢወስንም ቢያንስ 3 ወር መጠበቅ ይኖርብሻል። ይህም በአካልና በስነልቦና ዝግጁ እንድትሆኚ እድል ይሰጣል። በተደጋጋሚ ውርጃ ካጋጠመሽ ግን የማርገዝ ሙከራሽን አቁመሽ ህክምና መጀመር ይኖርብሻል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ