የቅድመ ወሊድ ክትትል

በእርግዝናቸው ወቅት ጥሩ የጤና እንክብካቤ ያገኙ ሴቶች በሰላም የመገላገልና ጤናማ ልጆች የመውለዳቸው እድል ከፍተኛ ነው። የቅድመ ወሊድ ክትትል የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፡-
  • የተስተካከለ የእርግዝና ሁኔታ መኖሩን ያረጋግጣሉ፤
  • የህፃኑን ዕድገት እና ጤና ለመከታተል ይችላሉ፤
  • እናትየዋም ሆነ ሕፃኑ/ኗ እንዳይታመሙ ቅድመ ጥንቃቄና መከላከል ለማድረግ ያስችላል፤ የእናትም ጤና እንዲሻሻል ያደርጋል። ለምሳሌ በእርግዝና ጊዜ የሚሰጠው አይረን/ፎሌት እንክብል የደም ማነስን ለመከላከል ይረዳል፣ የቲቲ ክትባት አዲስ የተወለደውን ሕፃን ከመንጋጋ ቆልፍ ለመከላከል ይረዳል።
  • ከእርግዝና ጋር የተያያዘ ከዚህ ቀደም ያጋጠመ ወይም ወደፊት ሊያጋጥም የሚችል የጤና ችግር ካለ በምርመራ ያውቃሉ። ችግሮቹንም በመለየት ለማከም ይረዳል። ለምሳሌ ወባን፣ ኤች አይ ቪንና የደም ግፊትን መመርመርና ተጨማሪ ችግር ከማምጣታቸው በፊት ማከም ያስችላል፤
  • ቤተሰብ በወሊድ ወቅት ዝግጅት እንዲያደርግና አደገኛ ምልክቶችን አውቆ ሲከሰቱ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ ለማድረግ ያስችላል፤
  • አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን ለመስጠት ጥሩ አጋጣሚ በመሆን ያገለግላል። ለምሳሌ፤ ወባን ለመከላከል በጸረ ወባ መድኃኒት የተነከረ አጎበርን መጠቀም፣ የኤችአይቪ ምክርና ምርመራ አገልግሎትን መስጠት፣ ኤች.አይ.ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ መከላከል፤
  • በጤና ተቋም የመውለድን ጥቅም ይማራሉ፤
  • ሴቶች ስለጡት ማጥባት፣ ከወሊድ በኋላ ስለሚደረግ የቤተሰብ ዕቅድ እና ስለ ተመጣጠነ አመጋገብ ምክር ያገኛሉ፤
  • በጤና ተቋም የመውለድን ጥቅም ይማራሉ፤
✸ የጤና ችግር ለሌለባት ወይም ላልገጠማት ሴት ስምንት የቅድመ ወሊድ ክትትል ጉብኝት ማድረግ አለባት፡፡ ተያያዥ ችግሮች ላሉባት ሴት ግን የሚያስፈልጋትን ያህል ጊዜ መታየትና መጎብኘት አለባት፤
prenatalcare
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ