የነብሰ ጡር አመጋገብ

በእርግዝና ወቅት ጤናማ አመጋገብ ሊኖርሽ ይገባል። ለሁለት ሰው እየበላሽ መሆንሽን አትርሺ። ለሁለት ሰው መብላት ማለት ግን ብዙ መብላት ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ማለት ነው።የተመጣጣኝ ምግብ ማነስ የልጁን እድገት ሲገታ ለናትየው ደግሞ ውስብስብ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። ከምትመገቢው ምግብ በተጨማሪ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እርግዝናን ጤናማ ከማድረግ አልፎ ምጥን ያቀላል። ማንኛውም ወደ ሰውነትሽ የሚገባ ነገር ወደልጅሽ ስለሚሄድና እንቅስቃሴ ማድረግ አካልሽን ስለሚያጠነክረው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች በደንብ ማንበብ ጤናማ እርግዝና እንዲኖርሽ ያደርጋል።
can-i-eat-turkey-while-pregnany

የተመጣጠነ ምግብ መመገብ

 • በሽታን እንድትቋቋሚና ጤናማ እንድትሆኚ ይረዳል፤
 • ጥርስና አጥንቶችሽን ጠንካራ ያደርጋቸዋል ይህም በእርግዝና ሰአት የሚከሰትን የድድ መድማት ሲከላከል ፅንሱን የመሸከምም ጉልበት እንዲኖርም ያደርጋል
 • ስራ ለመሥራት የሚያስችልሽን ኃይል ይሰጣል፤
 • ልጅሽ በእናቱ ማኅፀን ውስጥ በደንብ እንዲያድግ ይረዳዋል፤
 • ከወሊድ በኋላ በፍጥነት ጥንካሬሽ እንዲመለስ ያግዛል፤
 • ጤናማና የመማር ብቃት ያለው ሕፃን እንዲኖርሽ ያደርጋል፤

የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ(የምግብ እጥረት)

 • ደካማ ያደርጋል፣
 • አቅም ያሳጣል፣
 • በሽታን መቋቋም ያዳግታል፣ እንዲሁም ሌሎች ከባድ የጤና ችግሮችን ያስከትላል፤
 • የጽንስ መውረድን ሊያስከትል ይችላል፣
 • ሕፃኑ በጣም ትንሽ ሆኖ እንዲወለድ ወይም የአካል ጉዳት ይዞ እንዲወለድ ሊያደርግ ይችላል፤
 • ሕፃኑ ወይም እናትየዋ በወሊድ ጊዜ ወይም ከወሊድ በኋላ የመሞት እድልን ይጨምራል፤
እንዳባባሉም ከሆነ “የበላና የተማረ ወድቆ አይወድቅም” ነውና ለአመጋገብሽ ከፍተኛ ትኩረት ስጪ። የተፈቀዱና ያልተፈቀዱ ምግቦችን ለይተሽ አውቀሽ በስርአቱ ተግብሪ።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ