በኢትዬጵያ መንግስት ካለበት የጤና ሽፋን ችግር ባለፈ እናቶችና ህፃናት ህይወታቸውን እያጡ ያሉት መከላከልና ማዳን በሚቻሉ የጤና እክሎች ነው። እነዚህ እክሎች ተገቢውን የቅድመ ወሊድ፣ ድህረ ወሊድ እንዲሁም ወሊድ አገልግሎቶችን በጤና ተቋም በመውሰድ መቅረፍ የሚቻል ቢሆንም በ2015 የወጣው የአለም የጤና ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው አስፈላጊውን የቅድመ ወሊድ ክትትል ያደረጉ 32%፤ የድህረ ወሊድ ክትትል ያደረጉ 12%፤ እንዲሁም በሰለጠነ አዋላጅ የወለዱ እናቶች 16% ብቻ ናቸው። ይህን ቁጥር ለመጨመር መንግስት ማሻሻል ካለበት የአገልግሎት ሽፋንና ጥራት ቀጥሎ እናቶችንና ማህበረሰቡን ማስተማር ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።
ይህ ድህረገፅም ሆነ በተያያዥነት የተዘጋጁት የሞባይል መገልገያ (እናት መረጃ)፣ የFacebook group (እናት ቤተሰብ) እና የ Facebook page (እናት መረጃ) መረጃን ከማግኛና ከመወያያ መድረክ ባለፈ የዘለሉ አለመሆናቸውን በማወቅ ለግል የጤና ችግሮ ሁሌም ሀኪሞን ማማከር ይኖርቦታል።
አሁን ያለውንም ሆነ ወደፊት የምናስተላልፋቸው መረጃዎች ጥራት ለማረጋገጥ የራሳችን ጥረት ብናደርግም መረጃዎቹን አስታኮ ለሚከሰት ማንኛውም ችግር አዘጋጁ ሀላፊነት እንደማይወስድ እናሳውቃለን። ስለዚህም መረጃን ሲወስዱም ሆነ ሲያስተላልፉ የራስዎን ጥንቃቄ ያድርጉ።

እናት መረጃ

መዝጊያ