የእርግዝና ምልክቶችና ምርመራ

እርግዝና አካልንና አይምሮን በሚገባ የሚለዋውጥ የተፈጥሮ ኡደት ነው። እነዚህ ለውጦች በተለያየ የእርግዝና ወቅቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። አንዳንዶቹ እርግዝናው ተጀምሮ እስኪያልቅ ሲቆዩ የተቀሩት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ሊታዩ የሚችሉ ለውጦች ናቸው። ከነዚህ ለውጦች መካከል እርግዝና መፈጠሩን አስመልክቶ የመጨረሻው የወር አበባ በመጣ ከአራት ሳምንታት በኋላ ወይም እርግዝና ከተፈጠረ ሁለት ሳምንት በኋላ የሚከሰቱ ምልክቶች አንድ ሴት እርጉዝ ስለመሆኗ ፍንጭ ይሰጣሉ። እነዚህ ምልክቶች ታዲያ እንደየሰዉ ይለያያሉ። አንዲት ሴትም ብትሆን በተለያየ እርግዝና የተለያየ ምልክት ልታሳይ ትችላለች። ጥንቃቄ የጎደለው ግብረስጋ ግንኙነት ፈጽመሽ ከሆነና ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ምልክቶች ውስጥ አንቺ ላይ ያስተዋልሽው ምልክት ካለ እርጉዝ መሆንሽን በህክምና ማረጋገጥና የቅድመ ወሊድ ክትትል መጀመር ይኖርብሻል።

ማቅለሽለሽ

ማቅለሽለሽ የእርግዝና የመጀመርያዉና ዋነኛው ምልክት ነው። የማቅለሽለሽ ስሜቱ እርግዝና ከተከሰተ በኋላ ባሉት ሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ውስጥ ሲጀምር እስከ ማስመለስ ድረስ ሊደርስ ይችላል። በአብዛኛው ጊዜ ጠዋት ጠዋት ላይ ቢሆንም ስሜቱ የሚጠነክረው አንዳንድ ነብሰ ጡሮች በተለያየ ሰአት በቀን ውስጥ ሊያቅለሸልሻቸው ወይም ሊያስመልሳቸው ይችላል። ይህ የማጥወልወል ስሜት መንስኤው በውል ባይታወቅም የእናትየው ሰውነት ለእርግዝና በሚያደርገው ዝግጅት የሚመነጩ ፈሳሾች (ሆርሞኖች) ምክንያት የምግብ መፈጨት ሂደቱ ስለሚዳከም እንደሆነ ይገመታል። በእርግዝና ሰአት የሚከሰተውም የማሽተት አቅም መጨመር ለዚህ ስሜት የራሱን የሆነ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተለምዶ የሴት ወጉ በመባልም ይታወቃል።
penyebab-mual-saat-hamil-tua
aid1472219-v4-728px-Enjoy-Your-Final-Weeks-of-Pregnancy-Step-18

ድካም

ድካም እርግዝና በተከሰተ ሁለት ሳምንታት የሚጀምርና በአብዛኛው ጊዜ ከሶስት ወር በኋላ የሚቀንስ ስሜት ነው። ልጅ ለመሸከምና ለመመገብ በሚያደርገው ሽር ጉድ ሰውነትሽ ያልተለመደ ድካም ሊሰማውና እንቅልፍ እንቅልፍ ሊልሽ ይችላል። ይህ ድካምና የእንቅልፍ ስሜት ፅንሱ ሲረጋጋና የማቅለሽለሽ ስሜቱ ሲቀንስ አብሮ ቢቀንስም ከሰባተኛ ወር በኋላ በአብዛኛው ጊዜ በድጋሚ ይከሰታል። ይህ የሚሆነው የፅንሱ መጠን ስለሚጨምርና ሌሎች የእርግዝና ስሜቶች ተገቢዉን እንቅልፍ እንዳታገኚ ሊያረጉሽ ስለሚችሉ ነው።

የራስ ምታት

የራስ ምታት እርግዝና እንደተፈጠረ ከሚታዩ ምልክቶች ዋነኛው ነው። በአብዛኛው ጊዜ ቶሎ የሚታዩት የእርግዝና ስሜቶች ተደጋጋፊና ሰውነታችን በሚያመነጨው ሆርሞኖች(ፈሳሾች)ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው። እራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና የድካም ስሜት አንዱ ለሌላኛው መባባስ ምክንያት ናቸው።
mulher-gravida-com-uma-dor-de-cabeça-69736695
249aacc3a79c82cff2e7ed6cb09cd654

ቶሎ ቶሎ መሽናት

ከተለመደው በተለየ ቶሎ ቶሎ መሽናት ሌላኛው የእርግዝና ምልክት ነው። ልጅን በማህፀን መሸከምና መመገብ ለሰውነትሽ ተጨማሪ ስራ ነው። ሰውነትሽም ሆነ ልጅሽ የሚያስፈልገዉን ሃይል ለመስጠት የደም ዝውውርሽ ይጨምራል። የደም ዝውውርሽ ጨምሯል ማለት ኩላሊትሽ የሚያጣራው የፈሳሽ መጠን ይጨምራል ማለት ነው። ለዛም ነው ቶሎ ቶሎ ሽንትሽ የሚመጣው። ይህ የእርግዝና ስሜት ለዘጠኙም ወር የሚዘልቅና እየባሰበት የሚሄድ ይሆናል። ፅንሱ እየገፋ በሄደ ቁጥር የሽንት ፊኛሽን እየተጫነው ስለሚመጣ ወደ መጸዳጃ ቤት የምትሄጅበት መጠን ይጨምራል።

የምግብ አምሮት

የምግብ አምሮት በአብዛኛው እርጉዞች ላይ የሚከሰትና ሴቶችን የሚያዝናና የእርግዝና ምልክት ነው። በእርግዝና ወቅት አፍንጫሽ በተለየ መልኩ የማሽተት አቅሙ ሊጨምርና የምግብ አምሮትሽን ከፍ ሊያረገው ይችላል። በተቃራኒው ደግሞ የምትወጃቸውን ምግቦች ሊትጠዪ ትችያለሽ። ያማረሽ መጠጥም ሆነ ምግብ ላንቺና ለፅንሱ ጉዳት እስከሌለው ድረስ መውሰድ ትችያለሽ።
depositphotos_59074419-stock-illustration-pregnant-woman-craving-junk-food
feelings-clipart-mood-swing-14

የፀባይ መለዋወጥ

አሁን መሳቅ ደግሞ ማዘን ምንም ሳይቆዩ ማልቀስ እርግዝና ከሚያመጣችው ምልክቶች ግራ የሚያጋባው ነው። አዎ የፀባይሽ መቀያየር በአካባቢሽ ላሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ላንቺም ግራ ሊያጋባሽ ይችላል። ይህ የሚሆነው ከእርግዝና ጋር ተያይዘው የሚመነጩ ሆርሞኖችየአይምሮሽ የመልክት ማስተላለፊያ ክፍል ላይ ተፅዕኖ ስለሚያሳድሩ ነው። እርጉዝ መሆንሽ በህክምና ከተረጋገጠ በኋላ የማይለቅ የድብርት ወይም የጭንቀት ስሜት እየተሰማሽ ከሄደ የሃኪም እርዳታ ማግኘት አለብሽ። ።

የጡት መጨመርና መጠንከር

የወር አበባ ከመምጣቱ አንድ ሳምንት አስቀድሞ የሴት ልጅ ጡት የመጠጠርና የመወጠር ስሜት ያሳያል። ልክ የወር አበባ መፍሰስ ሲጀምር ወደነበረበት መጠንና ይዘት ይመለሳል። ፅንስ ከተፈጠረና የወር አበባው ከቀረ ግን የጡትሽ መጠን እየጨመረና ውስጡም እየጠጠረ ይሄዳል። ይህ ለውጥ ምናልባት ጥሩ ስሜት ላይፈጥርብሽ ብሎም ህመም ሊሰማሽ ይችላል። ይህ ልጅሽ ከተወለደ በኋላ ለሚያስፈልገው የእናት ጡት የመጀመርያው ዝግጅት ነው። በጊዜ ህመሙ ቢተውሽም መጠኑ ግን አይቀንስም። ከዚህም ጋር ተያይዞ የጡት ጫፍ ይጠቁራል።
Week4_Large
Constipationsdgsg

የሆድ ድርቀት

የሆድ ድርቀት የእርግዝና ሆርሞኖች የሚያመጡት አሉታዊ የእርግዝና ምልክት ነው። የምግብ ስርዓትን በማዳከም የሆድ ድርቀትን ያስከትላሉ። ከሆድ ድርቀቱ ጋር ተያይዞም የሆድ መወጠርና አየር የሞላው አይነት አስጨናቂ ስሜት ሊያመጣ ይችላል። ምንም እንኳን ስሜቱ ምቾትን የሚነሳ ቢሆንም አንቺም ሆነ ልጅሽ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አያደርስም።

የወር አበባ መቅረት

የወር አበባ መቅረት ለእርግዝና መከሰት ዋነኛው ምልክት ነው። በተለይ የወር አበባሽ ጊዜውን ጠብቆ የሚመጣ ከሆነና መምጣት ከነበረበት ጊዜ አንድ ሳምንት ካለፈው እርጉዝ የመሆን እድልሽ በጣም ሰፊ ነው። የወር አበባሽ ጊዜውን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ መቅረቱን እንደ ምልክት ማየት ይከብዳል። ሌላው ልብ ልትይው የሚገባ ነገር ፅንሱ ከተፈጠረ ከሁለት ሳምንት በኋላ የሚከሰትን የደም መፍሰስ ነው። ይህ የደም መፍሰስ የሚከሰትበት ወቅት የወር አበባ ከሚመጣበት ቀን ጋር ስለሚቀራረብ የወር አበባ ሊመስል ይችላል። ግን ይህ ፅንሱ ማህፀን ላይ መቀመጡን አስመልክቶ የሚፈስ ደም በመጠንም በከለርም ይለያል። ቢበዛ ከሶስት ቀን በላይ የማያልፍና መጠኑም ከወር አበባ እጅጉን ያነሰ ነው። ከለሩ ፈዘዝ ያለና መጠኑ የውስጥ ልብስሽን ከማቆሸሽ አያልፍም።
Manage-Your-Period-Step-6-Version-2
aid1591686-v4-728px-Induce-a-Period-Step-1

ምርመራ

ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መሃል ያስተዋልሽው ነገር ካለና እርጉዝ እሆናለው ብለሽ ከተጠራጠርሽ በህክምና ማረጋገጥ ይኖርብሻል አካባቢሽ መድሃኒት ቤት ካለ እቤትሽ ሆነሽ ምርመራውን ማረግ የምትችይበትን መሳሪያ መግዛት ትችያለሽ። እነዚህ መሳሪያዎች በሽንት ውስጥ የሚገኝን ኤች ሲ ጂ(hCG)የተባለ ሆርሞን መጠን በመለካት እርግዝና መፈጠሩንና አለመፈጠሩን ሲነግሩን የተለያየ አይነት የአጠቃቀም ዘዴ ሊኖራቸው ይችላል። ጊዜው እየገፋ ሲሄድ ወደ እንግዴ ልጅ የሚቀየሩ ህዋሶችም ናቸው ይህን ሆርሞን የሚያመነጩት። እንደ መመርመሪያው ጥራት የወር አበባሽ ከመቅረቱ አንድ ሳምንት አስቀድሞ እርግዝናን ማወቅ ይቻላል። ሆኖም የወር አበባ ከቀረ አንድ ሳምንት በኋላ የሚደረግ ምርመራ የተሻለ ውጤት ይሰጣል። ምርመራውን ጠዋት ከእንቅልፍሽ ስትነቂ ማረግም ይመከራል። ሌላኛው መንገድ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ መመርመር ነው። ሆስፒታልም ተመሳሳይ የሆነ የመመርመሪያ መንገድ ሲሆን የሚጠቀሙት ፅንሱ ሲገፋ ግን በአልትራ ሳውንድ መታወቅ ይችላል። ነብሰ ጡር መሆንሽን በየትኛውም መንገድ ካወቅሽ የቅድመ ወሊድ ክትትል መጀመር እንዳትረሺ። ስለቅድመ ወሊድ መረጃ፣ጥቅምና አገልግሎት አሰጣጥ ለማወቅ የቅድመ ወሊድ ክትትል የሚለውን ክፍል አንብቢ።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ