ማቅለሽለሽ

ከ6ኛ ሳምንት ጀምሮ እስከ 14ኛ ሳምንት ሲቆይ ከ8 እስከ10 ሳምንት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በአብዛኛዉ ጊዜ ከ3 ወር በኋላ ሲቆም አንዳንድ ነብሰጡሮች ላይ እስኪወልዱ ሊቆይ ይችላል፡፡

ማቅለያ መንገዶች
 • ጠዋት ጠዋት ከአልጋ ከመዉረድሽ በፊት ቀለል ያሉ ብስኩቶችን ወይም ቤት የተዘጋጀ ቂጣ በዉሃ በለስላሳ ወይም በጁስ መቅመስ።
 • ምግብ እየበላሽ መጠጥ አለመጠጣት
 • የድንች ጥብስ መብላትና ሎሚ በዉሃ መጠጣት
 • በቂ እረፍት ማድረግ
 • አንዴ ብዙ ከመብላት ትንሽ ትንሽ ቶሎ ቶሎ መብላት
የማስመለሱ መጠን ከፍተኛ ከሆነና ምግብ ዉስጥሽ መቀመጥ ካቃተዉ ወደ ጤና ማእከል መሄድ ይኖርብሻል።
penyebab-mual-saat-hamil-tua
aid1472219-v4-728px-Enjoy-Your-Final-Weeks-of-Pregnancy-Step-18

ድካም

ሰዉነትሽ አዲሱን ለዉጥ ለመልመድ በሚያረገዉ ሙከራ የድካም ስሜት ይመጣል፡፡ የደም ግፊትሽ ወይም የስኳር መጠንሽ ከቀነሰ የማዞር ስሜት ይኖራል፡፡

ማቅለያ መንገዶች
 • በቀስታ መንቀሳቀስ በተለይ ከመቀመጫ  ስትነሺ
 • አንድ ቦታ ብዙ አለመቆም /አለመቀመጥ
 • በቂ ፈሳሽ መዉሰድ
 • በቂ እረፍት ማድረግ
 • ትንሽ ትንሽ ቶሎ ቶሎ መብላት (አንዴ  ብዙ ከመብላት)
 • እንቅስቃሴን ማዘዉተር (ከመተኛትሽ አራት ሰዓት በፊት የእግር ጉዞ ለ30 ደቂቃ ማድረግ)
 • ቡና የምትጠጪ ከሆነ ማቆም
 • ስትተኚ ምቾትሽን መጠበቅ

የሆድ ህመም

የእርግዝና ሆርሞኖች የሆድ ድርቀትንና በአየር መወጠርን ያመጣሉ። ይህ የሚሆነዉ የምግብ መፈጨት ኡደቱ ስለሚዳከም ነዉ፡፡

የሆድ ድርቀት ማቅለያ መንገዶች
 • በቀን ከ8-10 ብርጭቆ የሚሆን ዉሀ መጠጣት
 • ፍራፍሬና ቅጠላ ቅጠሎችን ባገኘሽዉ አጋጣሚ መመገብ
 • ሻይ መጠጣት -በቀን ከአንድ ብርጭቆ በላይ መሆን ግን የለበትም
 • እንቅስቃሴ ማድረግ
✸ የሆድ ድርቀቱ ከበዛና ህመም ከፈጠረብሽ ወደጤና ተቋም በመሄድ ሆድ የሚያላላ መድኃኒት መዉሰድ ትችያለሽ፡፡ በሌላ በኩል ፅንሱ እያደገ ሲሄድ የሆድ እቃሽ ዉስጥ የሚገኙ ክፍሎች ቦታቸዉን ይለቃሉ። ይህ የዉጋት ህመምን ያመጣል ወይም ምቾትን ሊያሳጣሽ ይችላል፡፡

የሆድ ህመም ማቅለያ መንገዶች
 • ከተኛሽበት /ከተቀመጥሽበት ስትነሺ ቀስ ማለት
 • ህመም በሚሰማሽ ሰዓት በሞቀ ዉሃ ገላን መታጠብ
 • ስትተኚ ወገብሽና እግሮችሽ መሀል ትራስ ማድረግ
Constipationsdgsg
WeirdEarlyPregnancySymptoms08

የማቃጠል ስሜት (ቅርሻት)

የእርግዝና ሆርሞኖች ምግብ የሚጓጓዝበትን ፍጥነት በማዳከምና ለምግብ መፈጨት የሚያስፈልገዉን የጨጓራ አሲድ መጠን በመቀነስ ቅባትነት ያላቸዉ ምግቦች ወደ ሰዉነታችን እንዳይሰራጩ ያግዳሉ፡፡ እነዚህ ቅባቶች ወደ ላይ በመምጣት ደረትሽ ላይ የማቃጠል ስሜት ወይም ቅርሻት ይፈጥራሉ፡፡

ማቅለያ መንገዶች
 • ትንሽ ትንሽ ቶሎ ቶሎ መብላት (አንዴ ብዙ ከመብላት)
 • ፈሳሽ ነገር ከምግብ ጋር መዉሰድን ማስወገድ (እየበሉ አለመጠጣት)
 • የዝንጅብል ሻይ ወይም የፓፓያ ጭማቂ መጠጣት
 • እንደበሉ አለመተኛት
 • ስትተኚ የሚያስቸግርሽ ከሆነ ከፍ ያለ ትራስ ማድረግ
 • ቡና የምትጠጪ ከሆነ ማቆም
 • ቡና የምትጠጪ ከሆነ ማቆም
 • ስትተኚ ምቾትሽን መጠበቅ

የወገብ ህመም

እርግዝና በገፋ ቁጥር ሰዉነትሽ የጽንሱን ክብደት ለመሸከም በሚያረገዉ ጥረት ወገብሽ ላይ ጫና ያሳድራል፡፡ ከእርግዝና በፊት የወገብ ችግር ካለብሽ የህመም ስሜቱ የባሰ ሊሆን ይችላል፡፡

ማቅለያ መንገዶች
 • እንቅስቃሴን ማዘዉተር
 • ቀጥ ብሎ መቀመጥ
 • በምትተኚ ሰአት ወገብሽን የሚደግፍ ትራስ ማድረግ
 • አንድ ቦታ ብዙ አለመቀመጥ
ምጥ
sleep leg upward

የእግር ቁርጥማትና እብጠት

የደም ዝዉዉር መገታት የቁርጥማት ስሜት እግር ላይ ይፈጥራል። የደም ዝውውሩ የሚገታው ማህፀንሽ የደም ትቦዎች ላይ በሚያሳርፈው ጫና ምክንያት ነው።

ማቅለያ መንገዶች
 • በቂ ዉሀ መጠጣት
 • የተመጣጠነ ምግብ መመገብ በተለይ ፍራፍሬና ቅጠላ ቅጠሎችን
 • የእግር መንገድ ማዘዉተር
በሌላ በኩል የእርግዝና ሆርሞን የደም ትቦ እንዲሰፋ ሲያረግ ፅንሱ እየገፋ ሲሄድ ዳሌና እግር ላይ ያሉ የደም ትቦዎች ጫና ያድርባቸዋል፡፡ ይህ የደም ቱቦዎች እንዲወጠሩና እንዲያብጡ ያረጋል፡፡ እግርሽም አብሮ ያብጣል።

ማቅለያ መንገዶች
 • አንድ ቦታ ላይ ብዙ አለመቆየት (ብዙአለመቀመጥ /ብዙአለመቆም)
 • ባገኘሽው አጋጣሚ እግርን መስቀል/ከፍ ማረግ (ስትተኚም ስትቀመጪም)
 • ጠባብ ጫማዎች አለማድረግ
 • ብዙ ፈሳሽ መዉሰድ (ዉሀ ወይም ሻይ ከሎሚ ጋር)

የጡት ህመም

ወተት ለማምረት በሚደረገው ዝግጅት ጡት መጠኑ ይጨምራል እንዲሁም ጥንካሬው፡፡ የጡትሽ ጫፍም ሊጠቁር ይችላል፡፡

ማቅለያ መንገዶች
 • ምቾች የሚሰጥ የጡት መያዣ ማድረግ
 • ህመም ሲሰማሽ በሞቀ ውሃ መታጠብ
 • ፍሳሽ ካለው ፈሳሹን የሚመጥ ጨርቅ መጠቀም
Week4_Large
flu

ጉንፋን ወይም ብርድ

አብዛኛዉ ነብሰጡር በጉንፋንና ብርድ ይጠቃል፡፡ ይህ የተለመደና ህክምና የማያስፈልገዉ ነዉ፡፡ ነገርግን ሙቀትሽ በጣም እየጨመረ ከሄደ ወይም አደገኛ የሚባሉ ምልክቶች ከታዩብሽ ወደ ህክምና ተቋም ባፋጣኝ መሄድ ይኖርብሻል።

ማቅለያ መንገዶች
 • በቂ እረፍት ማድረግ
 • የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
 • በቂ ፍሳሽ መውስድ
 • ትኩስ ነገር መጠጣት
 • በሙቅ ውሀ መታጠብ
 • በንፁ ውሀ እንፋሎት መታጠን
ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስት መንገዶች ስትከተዪ ሙቀትሽ አለመጨመሩን አረጋግጪ። የሙቀት መጨመር ማስወረድን ያስከትላልና። ነገር ግን ህመሙ ከ10 ቀን በላይ ከቆየ ወይም ትኩሳት ካለሽ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብሻል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ