የእንሽርት ውሃ ማነስ

የእርሽርት ውሃ ለልጅሽ ህይወት መቀጠል አስፈላጊ ሲሆን ልጅሽን በመከላከል ለጡንቻ ፤ሳምባ፤ እጅና እግር፤ እንዲሁም ለስርአተ ምግብ አካላት እድገት አስተዋፅዎ ያደርጋል፡፡ ከፀነስሽ ከ 12 ቀን በኋላ የእርሽርት ከረጢት ይፈጠራል፡፡ ይህ የእርሽርት ከረጢት ከተፈጠረ በኋላ የእርሽርት ውሀ መመረት ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ እናትየው ከምትጠቀመው ውሀ መመረት ይጀምራል፡፡ ወደ 20 ሳምንት አካባቢ ሲሆነው የፅንሱ ሽንት ለእንሽርት ውሀ ዋንኛው ግብዓት ይሆናል፡፡ አንዳንዴ የዚህ ውሃ መጠን ያንስና (ከ 500 ml በታች ሲሆን) ለጤና እክል ይፈጥራል።

ምልክቶች

  • ከማህጸንሽ የሚወጣ ፈሳሽ
  • በቂ ክብደት አለመጨመር
  • ፅንሱ ማደግ ባለበት ፍጥነት አለማደግ

ማንን ያጠቃል

በአንዳንድ ምክንያቶች የእርሽርት ውሃ ሊያንስ ይችላል፡፡ ከነዚህም ውስጥ
  • የእንግዴ ልጅ ችግር ፡- የእንግዴ ልጁ በቂ ንጥረ ነገር ለፅንሱ ማድረስ ካልቻለ ፅንሱ በበቂ ሁኔታ የፈሳሹን ዑደት መጠበቅ አይችልም
  • በሽንት ቧንቧ ወይም በኩላሊት እድገት ላይ ፅንሱ ችግር ካለበት
  • የመውለጃ ጊዜ ካለፈ
  • እናትየው የደም ግፊት፤ ስኳር እና የመሳሰሉት ችግሮች ካሉባት
  • ሁለትና ከዛ በላይ ፅንስ መሸከም
  • የእርሽርት ውሃው የሚፈስ ከሆነ

ህክምና

የእንሽርት ውሃ ማነስ ከ 3-6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከተፈጠረ ውርጃን፣ ያለጊዜውመውለድን፣ የፅንስ ጉዳት ሲከፋ ፅንሱን የመግደል ሁኔታ ይኖራል። ከ 6 ወር በኋላ ከተፈጠረ የፅንሱ እድገት ሊያዘግምና በቀዶ ጥገና እንድትወልጂ ሊያስገድድሽ ይችላል። የእንሽርት ውሃ ማነስ ምንም አይነት መከላከያና ህክምና የሌለው የጤና እክል ነው።

Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ