የእንግዴ ልጅ አቀማመጥ

የእንግዴ ልጅ አቀማመጥ ችግር የሚያመጣው ከማህፀን የታችኛው ክፍል ላይ ሆኖ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የማህፀንን በር ሲከድን ወይም ሲሸፍን ነው፡፡ በምጥ ጊዜ የማህፀን በር መከፈት ሲጀምር የእንግዴውም ልጅ ከማህፀን ግድግዳ ላይ ሊላቀቅ ይችላል፡፡ ይህም ህመም የሌለው የደም መፍሰስ ሲያስከትል ፅንሱንም እናትየውንም አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ የእንግዴ ልጅ ፅንሱ ከእናቱ ጋር የሚገናኝበት በር ስለሆነ በተፈጥሮ ልጁ ወቶ በራሱ መተንፈስ እስኪችል ድረስ ከማህፀን ግርግዳ ላይ መላቀቅ የለበትም። ይህ ችግር ያጋጠማት ሴት በቀዶ ጥገና ለመውለድ ትገደዳለች።

ምልክቶች

ችግሩ የሚታወቀው ወይም የደም መፍሰሱ የሚከሠተው ከ6 ወር በኋላ ባለው ጊዜ ስለሆነ ቀድመሽ ምልክቱን የማየት እድል የለሽም፡፡ ነገር ግን ሀኪምሽ በሚያካሂደው የጤና ክትትልሽ ላይ በአልትራሳውንድ ምርመራ ሊያገኘው ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚከተሉትን ምልክቶች ተጋለጭነትሽን ስለሚያሰፉ ሀኪምሽን ማማከር አትዘንጊ፡፡ ይህም፡
  • ያለጊዜው የሚከሰት የምጥ ስሜት
  • የደም መፍሰስ (መጠነኛ ወይም ሲብስ ከፍተኛ)
  • የፅንሱ አቀማመጥ ትክክል አለመሆን
  • የማህፀን መጠን ከእርግዝናሽ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ትልቅ ከሆነ

ማንን ያጠቃል

  • ሲጋራ ወይም ሌሎች ሱሶች ያሉባትን ነብሰ ጡር
  • በእርግዝና ሰአት እድሜ ከ 35 አመት በላይ ከሆነና በተለይ የመጀመርያ እርግዝና ከሆነ
  • ተመሳሳይ እርግዝና አስቀድሞ ተፈጥሮ ከነበር
  • በቀዶ ጥገና ወልዳ የምታቅን ሴት
  • የማህፀን ቀዶ ጥገና አድርጋ ከነበር
  • መንታና ከዛ በላይ ፅንስ ከተሸከመች

ህክምና

አንዴ ይህ ምልክት ከታየብሽ ትክክለኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ለህክምና ጣቢያው ቅርብ ከሆንሽ ቤትሽ ሆነሽ እየተመላለሽ መታከም የምትችዪ ሲሆን ቤትሽ ርቀት ካለው ግን በህክምና ጣቢያው ተኝተሽ ህክምናሽን መከታተል ይኖርብሻል፡፡ ነገር ግን የማያቋርጥ የደም መፍሰስ ካጋጠመሽና በህክምና መቆጣጠር ካልተቻለ በአስቸኳይ በቀዶ ጥገና እንድትገላገይ ይደረጋል፡፡ ይህም የእርግዝና ጊዜውን ያማከለ አይደለም፡፡
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ