የልጅ እድገት ክትትል

በኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በታች ከሚሆኑት ሕፃናት ግማሾቹ በምግብ እጥረት በሽታ ሳቢያ እድገታቸው የተገቱ (Stunted) ሲሆኑ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከክብደት በታች (Under Weight) ናቸው። ከ80% በላይ የሚሆነው የምግብ እጥረት በአይን የማይታይ ነው፡፡ በከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናትን በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡ ይሁንና እነዚህ በምግብ እጥረት ከተጎዱት 1/5 የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ አንድ በከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጎዳ ሕፃን ስናይ አራት በመካከለኛ የምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናት አሉ እንደማለት ነው፡፡ በቂ ምግብ አለማግኘትና ህመም የምግብ እጥረት ቀጥተኛ መንስኤዎች ናቸው፡፡ ለዛም ነው አንድ ቤተሰብ የልጁን የእድገት ሁኔታ መከታተል ያለበት።
የልጅሽን እድገት መከታተልና ማጎልበት፡-
  • የእድገት መደነቃቀፍን (Growth Faltering) በጊዜ ለመለየት (በጣም ከመዘግየቱ በፊት)ይጠቅማል፤
  • የልጅሽን እድገት በማጥናት የእድገት መስመሩን ማየት ይቻላል፤
  • የችግሩን ምክንያቶች ለማወቅ ይረዳል
  • የሕፃኑን እድገት ለማሻሻል የሚያስችሉ ተገቢና ሊተገበሩ የሚችሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያስችላል።
የልጅሽን እድገት ለመከታተልና ለማጎልበት በየወሩ ክብደቱን መመዘን፣ ጤናማ ያልሆነ እድገት በግልጽ እንዲታይ ክብደቱን መመዝገብና ጤናማ ያልሆነ እድገት ሲታይ በጤና ባለሙያ እና በሌሎች ሙያተኞች ድጋፍ እንክብካቤን ማድረግን ያስፈልጋል። የምግብ እጥረት በሽታ አስከፊ ደረጃ ላይ ከደረሰና መታየት ከጀመረ ብዙ ጊዜ የመፍትሔ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አልፏል ማለት ነው። በተለይ ልጅሽ ከ2 አመት በታች እያለ ከፍተኛ የሆነ የአካላዊና አእምሮአዊ እድገት የሚያጎለብትበት ወቅት ስለሆነ እና ከ2 ዓመት እድሜ በፊት የሚከሰቱ ችግሮችን የሕፃኑ እድሜ 2 ዓመት ከሞላ በኋላ ለመቀልበስ ስለማይቻል በነዚህ ወቅት ከፍተኛ ትኩረት ማረግ ይኖርብሻል። የልጅሽን እድገት ጤነኛ ለማድረግ በየ 3 ወሩ የእድገት ምርመራ ማድረግ ይኖርብሻል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ