የጨቅላ-ህፃን-አደገኛ-ምልክት

በልጅሽ ላይ ከታች ከተዘረዘሩት ምልክቶሽ ውስጥ አንዱንም ምልክት ካየሽ ወደ ህክምና ተቋም ባፋጣኝ መሄድ ይኖርብሻል
 • መንዘፍዘፍ ወይም ራስን መሳት
 • ሲነካኩት ብቻ መንቀሳቀስ ወይም ቢነካኩትም አለመንቀሳቀስ
 • ጡት ፈፅሞ ወይም በደንብ አለመጥባት
 • ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ወይም ለመተንፈስ መቸገር (≥ 60 ሁለት ጊዜ)
 • በጣም ሲያተኩስ ወይም ባልተለመደ ሁኔታ ሲቀዘቅዝ (≥ 37.50 C ወይም < 35. 50 C)
 • ክብድቱ በጣም ትንሽ የሆነ ሕፃን: <1500 ግራም ወይም በሰባት ወሩ የተወለደ
 • የተነፋና የደረቀ ሆድ
 • የውስጥ እግር ወይም የመዳፍ ቢጫ መሆን:Jaundice
 • የቀላ የሚደማ ወይም የሚመግል እትብት
 • መግል የሚፈሳቸው ዐይኖች ወይም ያበጡ የዐይን ቆቦች
 • የሚጠባው ወተት በብዛትና ተገፍቶ መውጣት
 • ክብደት አለመጨመር
ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ውጪ ልጅሽ ጤነኛ እንዳልሆነ እየተሰማሽ ከሆነ ከእናት ስሜት የሚበልጥ ነገር የለምና ወደጤና ተቋም ውሰጂው። ወደህክምና ተቋም በምትሄጂ ሰአት ጡት ማጥባትሽን እንዳታቆሚ። በተጨማሪም ተገቢ ሙቀት እንዲያገኝ በማድረግ ከተጨማሪ ችግሮች ልጅሽን ጠብቂ።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ