ያንቺ ግዴታዎች

በእርግዝናሽ ሰአት ካንቺ የሚጠበቁ ሃላፊነቶችን መወጣት ይኖርብሻል። ለጤናማ እርግዝና የሚያስፈልጉ እንክብካቤዎች እንዳሉ ሁሉ የሚከለከሉ ተግባራትም አሉ። በባህላችን እንደ ቀላል ነገር የሚታዩና የሚታለፉ የቀን ተቀን ተግባሮች ጉዳት ሊያመጡ ስለሚችሉ ከሌላ ጊዜ በላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

የሚበረታቱ ልምዶች

 • ጥሩ አመጋገብ (የተመጣጠነ ምግብ መመገብ)
 • ብዙ እረፍት ማድረግ፣
 • ከባድ ሥራዎችን አለመሥራት፣
 • ቀላል እንቅስቃሴ ማድረግ፣
 • የግል ንጽሕናን መጠበቅ (ንጹሕ መሆን)፣
 • ወባ ያለበት አካባቢ ከሆነ የፀረ ወባ ትንኝ መድኃኒት በተነከረ አጎበር ሥር መተኛት
 • የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግና በጤና ተቋም መውለድ
 • በሃኪም የሚሰጡ ተጨማሪ ማእድናትን በትክክል መውሰድ
 • የመንጋጋ ቆልፍ ክትባትን መከተብ
 • የኤች አይ ቪና ያባላዘር በሽታ ምርመራ ማረግና የበሽታው ተጠቂ ከሆኑ ህክምናን መከታተል
 • አደገኛ ምልክቶችን ሲያዩ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ

ጎጂ የሆኑ ልማዳዊ ድርጊቶች

 • አደንዛዥ እፆችን መጠቀም፣
 • አልኮል ቡናና ሻይ መጠጣት፣
 • ሲጋራን ማጤስ፣
 • መርዛማ ኬሚካሎች አካባቢ መገኘት
 • በሀኪም ያልታዘዘ መዳኒት (ባህላዊ መዳኒትን ጨምሮ)መውሰድ
 • ተላላፊ በሽታ ከያዘው ሰው ጋር ቅርበት መፍጠር
 • ባህላዊ ልምዶችን ለሃኪም ሳያማክሩ ማከናወን
 • የእንስሳት ቤትን ማፅዳት
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ