ደም ማነስ

በተለምዶ የደምማነስ የሚባለው የቀይ የደም ህዋስ ብዛት ማነስ ሲሆን ከእርግዝና ጋር ተያይዘው ከሚመጡ ችግሮች ዋነኛውና የተለመደው ነው። የቀይ ደም ህዋስ ማነስ በአይረን፣ በፎሌትና በቫይታሚን ቢ12 እጥረት የሚከሰት ሲሆን ይህ የቀይ ደም ህዋስ ማነስ ሰውነት በቂ ኦክስጅንን ለሰውነታችን ብሎም በእርግዝና ሰአት ለፅንሱ እንዳይደርስ ያደርጋል። ከማእድን እጥረት በተጨማሪ በእርግዝና እና ወሊድ ሰአት ብዙ ደም መፍሰስም ለዚሁ ችግር ያጋልጣል።

ምልክቶች

 • የገረጣ ቆዳና ከንፈር
 • ድካምና አቅም ማጣት
 • የማዞር ስሜት
 • ትንፋሽ ማጠር
 • የልብ ምት መፍጠን
 • ነገሮችን ማስተዋል አለመቻል

ማንን ያጠቃል

እርጉዝ ሴት ከሚያስፈልጋት መጠን አንፃር ሲታይ አብዛኛው ነብሰጡር ሴቶች የቀይ ደም ሴል እጥረት ያጋጥማቸዋል። ሆኖም ግን ማነሱ ሊበረታ የሚችለው
 • መንታና ከዚያ በላይ ሲረገዝ
 • በላይ በላይ ከተረገዘ
 • በእርገዝና ወቅት የምግብ መቆየት ችግር ካለ (ማስታወክ ከበዛ)
 • በልጅነት ሲረገዝ
 • በአይረን፣ በፎሌትና በቫይታሚን ቢ12 የበለፀገ በቂ ምግብ ካልተወሰደ
 • ከእርግዝናም በፊት ችግሩ ከነበረ

ህክምና

የቀይ የደም ህዋስ ብዛት ማነስ ያለጊዜው መውለድን፣ ከሰው ደም ወቀበልና ከወሊድ በኋላ ድብርትን በናትየው ላይ ሲያስከትል በፅንሱ ላይ የእድገት መገታትን ብሎም የቀይ የደም ህዋስ ብዛት ማነስን ያስከትላል። ለዛም ሲባል ከመጀመርያው የቅድመ ወሊድ ቀጠሮሽ ጀምሮ የደም ምርመራ ይደረግልሻል። የመጀመርያው ውጤትሽ ጥሩ ቢሆንም ምልክቶችሽ እየታዩ ቀጣይ ቅድመ ወሊድ ቀጠሮዎችሽም ላይ ተጨማሪ ምርመራ ይደረግልሻል። የቀይ የደም ህዋስ ብዛት ማነስ ካለብሽ የፎሊክ አሲድና የአይረን ማእድ የያዘ እንክብል እንድትወስጂ ይሰጠሻል። በተጨማሪም በጠፈጥሮ በአይረን፣ በፎሌትና በቫይታሚን ቢ12 የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ይኖርብሻል። ለበለጠ መረጃ የነብሰጡር አመጋገብ የሚለውን መረጃ አንብብቢ። በቀላሉ ልትቆጣጠሪው የምትችይው ችላ ካልሽው ግን አንቺንም ልጅሽንም ዋጋ የሚያስከፍል የጠና እክል ነውና ትኩረት ልትሰጪው ይገባል።
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ