ጡት ማለብ

አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የጡት ወተትን ማለብ እናት ልጅዋን የጡት ወተት መመገብን እንድትቀጥል ያስችላታል። የታለበ የጡት ወተት በቤት ውስጥ ሙቀት በንጹህ ስፍራ ለስምንት ሰዓት እንዲሁም በማቀዝቀዣ (Refrigerator) ውስጥ ደግሞ ለ24 ሰዓት ሳይበላሽ መቀመጥ እና ለሕፃኑ ሊሠጥ ይችላል። ጡትን ማለብ በሚከተሉት ጊዜያቶች ሊጠቅም ይችላል፡፡
 • እናት ከቤት ስትወጣ የጡት ወተቷን ለሕጻኑ ትታ እንድትሄድ ያስችላታል (ይህ በተለይ በሥራ ምክንያት የጡት ማጥባትን ለሚያቋርጡ እናቶች ትልቅ ጠቀሜታ ይሰጣል)
 • ሲወለዱ ዝቅተኛ/በጣም ዝቅተኛ ክብደት ኖሮዋቸው ጡት መያዝ ለማይችሉ ሕፃናት የጡት ወተት ለመስጠት ያመቻል፡፡
 • በሕመም ምክንያት ጡት መሳብ ለማይችሉ ሕፃናት የጡት ወተት በማንኪያ/ስኒ/ኩባያ ለመስጠት ያስችላል፡፡
 • ከጡት መጥባት ጋር ተያየይዘው የሚመጡ ችግሮችን ለመከላከል ይረዳል፡፡

የጡት ወተትን እንዴት ማለብ ይቻላል

 • እጅን በደንብ በሳሙናና በውሃ መታጠብ
 • ለወተት ማለቢያ የሚሆነዉን ዕቃ በደንብ ማጠብና እና መቀቀል
 • በአመቺ ሁኔታ በመቀመጥ የማለቢያውን ዕቃ ወደጡት አስጠግቶ መያዝ
 • አንዳንዴ ጡትን ማሻሸት እና ሙቀት የሚሰጥ ልብስ መልበስ የጡት ወተት በደንብ እንዲፈስ ይረዳል
 • የአውራ ጣትን በጡት ጫፍ ዙሪያ ካለው ጥቁር ክብ በላይ እና ሌሎቹን ጣቶች በጡት ጫፍ ዙሪያ ካለው ጥቁር ክብ በታች ማድረግ
 • አውራ ጣትን እና የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጣቶች ወደ ደረት ጫን ወይም ገፋ ማድረግ፡፡ በመቀጠል ቀስ አድርጎ ወደ ጥቁሩ የጡት ክፍል ጫን ወይም ገፋ ማድረግ፡፡
 • ጣቶችን በጡት ላይ ከብለል ማድረግ
 • ወተቱ መፍሰስ ሲጀምር ጠብ ጠብ እያለ ወይም በደንብ ሊፈስ ይችላል፡፡. የሚፈሰዉን ወተት በንጹህ ዕቃ ላይ ማጠራቀም፡፡
 • ከመጠን በላይ ጡትን ማሸት የጡቱን ቆዳ እንዲቆጣ እና እንዲቆስል ያደርጋል፡፡ የጡት ጫፍን መጭመቅ ወተት እንዳይፈስ ያደርጋል፡፡
 • አውራ ጣትን እና የሌባ ጣትን በጡት ዙሪያ እያንቀሳቀሱ በመጫን እና በመልቀቅ ወተት ከሁሉም የጡት ክፍሎች እንዲፈስ ማድረግ፡፡
 • አንደኛውን ጡት ከ3 እስከ 5 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ እና የሚወጣው ወተት እስኪቀንስ ድረስ ማለብ እና ወደ ሌላኛው ጡት መዛወር ከዛም ሌላውን ጡት ደግሞ ማለብ (በአጠቃላይ ከ20-30 ደቂቃ ሊፈጅ ይችላል)
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ