ፕሪ-ኢክላምዢአ

በነፍሰ ጡር እናቶች ላይ ብቻ የሚከሠት ሲሆን ምልክቶቹም የደምግፊት በድንገት በከፍተኛ ፍጥነት መጨመርና በሽንት ውስጥ የፕሮቲን መታየት ከምልክቶቹ ውስጥ ናቸው፡፡ እርግዝናሽ ወደ 20ኛው ሳምንት አካባቢ ይፈጠራል፡፡ ፕሪ-ኢክላምዢዓ ከፍተኛ የደም ግፊትን የሚያስከትል ቢሆንም የደም ግፊት አለብሽ ማለት ግን ፕሪ-ኢክላምዢዓ አለብሽ ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ የሌላ ነገር ምልክት ግን ሊሆን ይችላል፡፡ በበሽታው ተጠቅታ ግን ቶሎ ህክምና ያላገኘች እናት ለጉበት፣ ለኩላሊት እና ከልብ ጋር ለተያያዙ ችግሮች ተጋላጭ ልትሆን ትችላለች። ከዚህም ሲያልፍ ለሒውት አስጊ ለሆነውና ከእርግዝና በኋላ ለሚፈተረው ኢክላምዢዓ በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል። ከናትየው አልፎ ፕሪ-ኢክላምዢዓ በቂ ደም ወደፅንሱ እንዳሔድ በማገድና ፅንሱ በቂ ምግብና ንፁህ አየር እንዳያገኝ በመከልከል የፅንሱን ተፈጥሮዓዊ እድገት ይገታል። ለዛም ነው ፕሪ-ኢክላምዢዓ ያለባቸው እናቶች ክብደቱ ዝቅተኛ የሆነ ልጅ የሚወልዱት።
 • ነገርግን ፕሪ-ኢክላምዢዓ ቶሎ ከታወቀና በበቂ ሁኔታ የቅድመ ወሊድ ክትትል ከተደረገለት እናትየውም ላይ ሆነ ፅንሱ ላይ አደጋ የማድረስ እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡

ምልክቶች

ደረጃ አንድ(ቀላል)ፕሪ-ኢክላምዢዓ ምልክቶች:
 • ከፍተኛ የደም ግፊት
 • በሽንት ውስጥ የፕሮቲን መታየት
 • ውሃ አለመጥማት
ደረጃ ሁለት(ከባድ)ፕሪ-ኢክላምዢዓ ምልክቶች ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ:
 • የራስ ምታት
 • የእይታ መደብዘዝ
 • የእጅ ፣ የፊት ወይም የእግር ማበጥ
 • ከመጠን በላይ ክብደት መጨመር
 • ብርሃንን መቋቋም አለመቻል
 • ድካም (ማስታወክ)
 • የሽንት ማነስ
 • የአተነፋፈስ ችግር
 • በቀላሉ ለተለያዩ ህመሞች መጋለጥ
 • የሆድ ህመም
✸ ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩብሽ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብሻል።

ማንን ያጠቃል

 • የመጀመሪያ እርግዝና ከሆነ
 • አስቀድሞ በነበሩ እርግዝናዎች ለ ፕሪ-ኢክላምዢዓ ተጋላጭ የነበረች ነብሰ ጡር
 • ቤተሰብ ውስጥ (እናት ወይም እህት)በእርግዝና ወቅት ለ ፕሪ-ኢክላምዢዓ ተጋላጭ ከነበሩ
 • መንታ ወይም ከዚያ በላይ ያረገዘች ሴት
 • ከ 20 አመት በታች ወይም ከ40 አመት በላይ የሆናት ነብሰ ጡር
 • ከእርግዝና በፊት የደም ግፊት ወይም የኩላሊት በሽታ ያለባት ነብስ ጡር
 • ያልተመጣጠነ የሰውነት ውፍረት ያላትን ሴት

መከላከያ መንገዶች

በህክምና የተረጋገጠ መከላከያ ባይኖረም ለከፍተኛ የደም ግፊት የሚያጋልጡ ነገሮችን ግን መቆጣጠር ይቻላል። ከነዚህም ውስጥ፦
 • የጨው መጠን መቀነስ
 • ከ 6 – 8 ብርጭቆ ውሀ በቀን መውሰድ
 • በቂ እረፍት ማድረግ
 • በቋሚነት የሠውነት እንቅስቃሴ ማድረግ
 • የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ
 • እግርሽን በቀን ለተደጋጋሚ ጊዜ ከፍ ማድረግ
 • በተጨማሪም ሁልጊዜም ሀኪምሽ የሚነገርሽን የአመጋገብና የሰውነት እንቅስቃሴ በአግባቡ መተግበር አለብሽ፦ ያንቺም የልጅሽም ደህንነት በእጅሽ ነው።

ህክምና

የቅድመ ወሊድ ክትትል የምታደርጊበት ቦታ የደም ግፊትሽን ፣ የሽንት መጠንን እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ሙሉ የደም ምርመራ ይደረግልሻል፡፡ በሽታው ካለብሽ የበሽታውን ደረጃና የመውለጃ ቀንሽን ያማከለ ህክምና ይሰጥሻል። የመወለጃ ቀንሽ ከደረሠና ልጅሽ በበቂ ሁኔታ ካደገ ሀኪምሽ ልጁን በተቻለ መጠን እንድትወልጂ ያደርግሻል፤ ይህም በምጥ ወይ ደሞ አብዛኛውን ጊዜ በቀዶ ጥገና ሊሆን ይችላል። ደረጃ አንድ(ቀላል)ፕሪ-ኢክላምዢዓ ከሆነና ፅንሱ በበቂ ሁኔታ ካላደገ ሀኪምሽ የሚከተሉትን እንድታረጊ ይመክርሻል፦
 • በግራሽ በኩል በመተኛት እረፍት እንድታረጊ – ይህን ማረግ የፅንሱን ክብደት ከዋናዎቹ የደምስሮች እንዲርቁ ይረዳል
 • የቅድመ ወሊድ ክትትልሽ መጠን ይጨምራል
 • በምግብ ውስጥ የምትጠቀሚውን የጨው መጠን መቀነሥ
 • በቀን ቢያንስ 8 ብርጭቆ ውሀ መውሰድ
ደረጃ ሁለት(ከባድ)ፕሪ-ኢክላምዢዓ ከሆነና ፅንሱ በበቂ ሁኔታ ካላደገ ሀኪምሽ የደም ግፊት ህክምናዎችን ያደርግልሻል፡፡ አንቺ ላይ ጉዳት ሳይደርስብሽ መውለድ የምትችይበት ደረጃ ላይ እስክትደርሺ ድረስም በሆስፒታል ተኝተሸ የአመጋገብ ለውጥ እየተደረገልሽ ክትትልሽን ትቀጥያሽ፡፡
Share on facebook
Share on google
Share on twitter

አስተያየት

መዝጊያ